የአማራ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡- አቶ እርዚቅ ኢሳ የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ሰውበሰው ብዙአየሁ ደግሞ የክልሉ ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
ምክር ቤቱ ለንጋት ኮርፖሬት የቦርድ አመራር ሹመቶች ያጸደቀ ሲሆን÷ አቶ ስዩም መኮንን የቦርድ ሰብሳቢ እና ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ደግሞ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ምክር ቤቱ ለአራት ቀናት በነበረው ቆይታ÷ “የተሻሻለው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ” እና “የተሻሻለው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ማቋቋሚያ አዋጅ” አጽድቋል፡፡
እንዲሁም÷ 95 ነጥብ 31 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የክልሉን መንግሥት የ2015 በጀትም አጽድቋል፡፡
የተያዘው በጀት÷ በህወሓት እና በሸኔ የሽብር ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ለግብርና ኢንቨስትመንት፣ ለማዕድን ዘርፍ እና ለአካባቢ ጥበቃ ሥራ ትኩረት መስጠቱ ተመላክቷል፡፡
በምንይችል አዘዘው
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!