የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ በ3 የትምህርት ተቋማት መካከል ስምምነት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በጥናትና ምርምር ለመደገፍ በሶስት የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ስምምነት ተደረገ።
ተቋማቱ ጥናትና ምርምሩን የሚያስተባብር የጋራ ግብረ-ሃይል ማቋቋማቸው ነው የተገለጸው፡፡
ግብረ-ሃይሉን ያቋቋሙት የኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳና ሩዋንዳ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ÷በአፍሪካ የሚከሰቱ ችግሮች በአፍሪካውያን እንዲፈቱ በጥናትና ምርምር የተደገፈ እገዛ ያደርጋሉ ተብሏል።
የጋራ ግብረ-ሃይሉን ያቋቋሙት ከኢትዮጵያ የጎንደር፣ ከዩጋንዳ የማኬሬሬ እና ከሩዋንዳ የኪጋሊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትመሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ተቀማጭነቱ ደቡብ አፍሪካ የሆነው ፎርት ሀሬ ዩኒቨርሲቲም የጋራ ግብረ-ሃይሉን ስራ እንደሚያስተባብር ተጠቁማል፡፡
ተቋማቱ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ለመስጠት በጋራ እንደሚሰሩ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡