Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ሊያደርጉት የነበረው ተጠባቂ ጨዋታ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ።

ጨዋታው የተራዘመው የግሪኩ እግር ኳስ ክለብ ኦሊምፒያኮስ ባለቤት ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ በትናንትናው ዕለት በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው።

ኦሊምፒያኮስ ከአርሰናል ጋር በዩሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የመልስ ጨዋታ በኢሚሬትስ ስታዲየም መጫወታቸው ይታወሳል።

በወቅቱም የተወሰኑ የአርሰናል ተጫዋቾች ከግሪኩ ክለብ ባለቤት ጋር ግንኙነት ነበራቸው ነው የተባለው።

ይህን ተከትሎም ጨዋታው እንዲራዘም የተደረገ ሲሆን፥ ከእርሳቸው ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተጫዋቾችም ወደ ጨዋታ ከመመለሳቸው በፊት ለሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ ይደረጋል ተብሏል።

ጨዋታው ለምን ያክል ጊዜ እንደተራዘም ግን የታወቀ ነገር የለም።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.