Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች የሚያደርገው እርዳታ ተጠናክሮ ቀጥሏል – ዶክተር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የክልሉ ነዋሪዎች የሚያደርገውን ሰብአዊ እርዳታ አጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ  ገለጹ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም መንግስት በትግራይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች እንዲሁም በአፋርና አማራ ክልሎች አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ አጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ወገኖችን ለመታደግ መንግስት በወሰደው እርምጃ ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ብቻ በተለያዩ አጋር ድርጅቶች ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ እርዳታ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ከ234 ሜትሪክ ቶን በላይ መድኃኒት ወደ ክልሉ መላኩንም አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈም ከ155 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ ነክ፣ ከ18 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ እርዳታን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎች ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ መደረጉንም ተናግረዋል።

987 ሺህ 137 ሊትር ነዳጅ ለ5 ነጥብ 2 ሚሊየን ትግራይ ክልል ነዋሪዎች በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

በየብስ ትራንስፖርት የሰብዓዊ እርዳታ በማጓጓዝ መቐለ ከደረሱ 4 ሺህ 323 ከባድ ተሸከርካሪዎች ውስጥ እስካሁን የተመለሱት 2 ሺህ 820ዎቹ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.