ተሸናፊው ውርስ ችግር ሊያሳምመን እንጂ ሊያሸንፈን አይችልም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተሸናፊው ውርስ ችግር ሊያሳምመን እንጂ ሊያሸንፈን አይችልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትዮጵያ ከነባር ችግሮቿ ተላቅቃ በተስፋዋ ጎዳና እንድትገሠግሥ እየታገልን ነው ብለዋል፡፡
ያለፈው ችግሯ ውርስም መከራችንን ሊያረዝመው ይታገለናል፤ እኛ ደግሞ ተስፋችንን ለማለምለም እንታገላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ በችግራችን ከተዋጥን ይነግሥብናል፤ ለተስፋችን ከታገልን ደግሞ እንነግሥበታለን ብለዋል፡፡
ተሸናፊው ውርስ ችግር ሊያሳምመን እንጂ ሊያሸንፈን አይችልምም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመልዕክታቸው፡፡
በዚህ እሑድ ሁላችንም መቻቻልና አብሮነት እንዲያሸንፍ እንጸልይ÷ ነጋችን ብሩህ እንዲሆን ደግሞ ወጥተን ዛፎችን እንትከል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!