Fana: At a Speed of Life!

የተባባሩት ዓረብ ኤምሬቶች የንግድ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የተባባሩት ዓረብ ኤምሬቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከርና ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰራ የአገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ገልጿል፡፡
አምባሳደር አክሊሉ ከበደ በተባባሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሻርጃ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ሊቀመንበር ከሆኑት አብደላ ሱልጣን አል ኡወይስ ጋር የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኘነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር አብደላ ሱልጣን አል ኡወይስ በሚኖራቸው ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር በትብብር በመስራት የየሀገሮቻቸውን የንግድ ስራ ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡
አምባሳደር አክሊሉ በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያና በተባባሩት ዓረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ማህበረሰብ በተለይም በሻርጃ ቢዝነስ ማህበረሰብ መካካል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ዋና ተልዕኳቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።
አጋር ከሆነው የሻርጃ የንግድ ምክር ቤት ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎትም አብራርተዋል፡፡
አምባሳደሩ አያይዘውም ከዚህ ቀደም የሻርጃ ንግድና ኢንዱስትሪ ቻምበር ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን አስታውሰዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ብቁ እና ተወዳደሪ እንዲሆን የሚያስችል የሙያ፣ የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ስልጠና፥ ሙያዊ ድጋፍና የልምድ ልውውጥ በሚደረግባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
በቀጣይ ጊዜ በወይይቱ በተነሱ የጋራ ጉዳዮች፣ የቢዝነስ ፕሮሞሽንና የመረጃ ልውውጥ ዙሪያ ከቀድሞ በተሻለ ደረጃ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ከዱባይ እና ሰሜን ኢሜሬትስ ቆንፅላ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.