በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጥሮ ፀጋዎችን ለማልማት የመንግስት ድጋፍ እንዲጠናከር ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማት የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን የፌደራል መንግስት ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ ተጠየቀ።
በስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና በቤኒሻጉል ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ ልዑክ በአሶሳ ከተማ የተለያዩ ተቋማትን መጎብኘቱን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡