ኮሮና ቫይረስን የሰጉት ፕሬዚዳንት ከመጨባበጥ የእግር ሰላምታን መርጠዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ እና የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪው ማሊም ሰይፍ ሸሪፍ ያልተለመደ ሰላምታ ልውውጥ ብዙዎችን ፈገግ አሰኝቷል።
የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ከማሊም ሰይፍ ሸሪፍ ሐማድ ጋር የእግር ሰላምታ ተለዋውጠዋል።
ምስሉን የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አጋርቶት በርካቶች ተቀባብለውታል።
የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ንክኪን ማስወገድ እንደሚገባ ለዜጎቹ አጽንኦት ሰጥቷል።
የፕሬዚዳንቱ ሰላምታም የሚኒስቴሩን መልዕክት ታሳቢ ያደረገ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።
ታንዛኒያን ጨምሮ የዓለም መንግስታት ቫይረሱን ለመከላከል መተቃቀፍ፣ መሳሳም እና ማንኛውንም የእጅ ሰላምታ አስወግዱ በማለት ተማፅኖ እያቀረቡ ነው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ