Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኢንተርኔት ልማት ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ኢንተርኔት ልማት ጉባዔ በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ጉባዔ የአፍሪካ ኢንተርኔት ሶሳይቲ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ያዘጋጀው ሲሆን፥ እስከ የካቲት 26 2012 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል።

በኢንተርኔት ልማት ጉባዔው ላይም በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የግል ሴክተር ድርጅቶች፣ የዘርፉ ምሁራን እና የሲቪል ማህበራት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ጉባዔው በቆይታው በሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ጥራት እና ተደራሽነት ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮችን እና ችግሮችን ለይቶ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

የሀገር ውስጥ የኢንተርኔት መሰረተ ልማቶችን በማሻሻል ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ የኢንተርኔት መሰረተ ልማቶችን በተሻለ መልኩ ለመጠቀም የሚያስችሉ የቴክኒክ አማራጮችንም በመለየት እንደሚመክር ታውቋል።

ለሁለት ቀናት ቀጥሎ የሚካሄደው ጉባዔው በኢትዮጵያ ምቹ የሆነ የኢንተርኔት ስነ ምህዳር እንዴት መፍጠር ይቻላል የሚለው ላይ ምክረ ሀሳቦችን በማስቀመጥ አንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.