ወጣቱ በአገራዊ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱ በአገራዊ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ከአመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ነዋሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ ማህበረሰብ አንቂዎችና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረኮችን አካሂዷል።
በመድረኩ ላይም የሀገር ጉዳይ የሁሉም ዜጎች ጉዳይ መሆኑን በመረዳት በተለይም ወጣቱ በአገራዊ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በውይይቱ የፌደራልና የግል ተቋማት በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው እና በአስተዳደሩ ስር ከሚገኙ የመንግስት ተቋማት ጋር በቅንጅት ስራዎችን በመስራት የህብረተሰቡን መሰረታዊ ችግር መፍታት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡
በድሬዳዋም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚፈጠሩ ችግሮች ጥናትና ምርምር ማድረግ እና የቅድመ መከላከል ስራዎችን መስራት ከፍተኛ ጥቅም እንደሚያስገኝ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
በመድረኩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና የካቢኔ አባላት መገኘታቸውን ከድሬዳዋ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡