Fana: At a Speed of Life!

ትዊተር ሰራተኞቹ ቤት ውስጥ ሆነው እንዲሠሩ  አዘዘ

አዲስ አበባ፣የካቲት 24፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትዊተር የኮሮቫ ቫይረስ ስርጭትን ለማስቆም ሰራተኞቹ ከቤታቸው ሳይወጡ ስራቸውን እንዲያከናውኑ  ማዘዙ  ተሰምቷል፡፡

ተቋሙ በሆንግ ኮንግ ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ  የሚገኙ ሰራተኞቹ  ቤት ውስጥ ሆነው መስራት  ግዴታቸው  መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 5 ሺህ ሠራተኞች ወደ ሥራ ሳይገቡ ስራቸውን ቤት ውስጥ እንዲያከናውኑ እንደሚያበረታታም አስታውቋል።

ለዚህም ትዊተር ሰራተኞቹ ለተወሰነ ጊዜ ከቤት ሆነው ለመስራት  የሚያስችላቸውን መንገዶች ማመቻቸቱ ተጠቁሟል።

የትዊተር የሰው ሃብት ሃላፊ ጄኒፈር ክሪየር÷የውሳኔያቸው ዋና አላማ በተቋሙ ሰራተኞች እና በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት  ዝቅ  እንዲል ማድረግ ነው ብለዋል።

የትዊተር እርምጃ የኮሮና ቫይረስ በእስያ ሀገራት መስፋፋቱን ተከትሎ ሌሎች ኩባንያዎች ከወሰዱት እርምጃ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተነግሯል።

ከኮረና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ጋር ተያይዞ ፌስቡክ እና ጉግልን ጨምሮ ሌሎች ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በአሜሪካ ውስጥ ስብሰባዎችን ለሌላ ጊዜ  ማስተላለፋቸውና መሰረዛቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.