ብሄራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር በውጪ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የተለየ ርብርብ ማድረግ ይገባቸዋል – አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር፣ የአገራችንን ተደማጭነት ለማጠናከርና ተደራሽነታችንን ለማስፋት በሀገር ውስጥና በውጪ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ከምንጊዜውም የተለየ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።
አቶ ደመቀ ዲፌንድ ኢትዮጵያ የአውሮፓ ግብረ ሀይል የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት በክብር እንድግነት ተገኝተው እንደተናገሩት፥ በተለያየ መልኩ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ጥረት በሚደረግበት ወቅት ዲፌንድ ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች መፈጠራቸው የኢትዮጵያን ድምጽ ለማሰማት ወሳኝ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ተቋሙ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር እያከናወናቸው ስላሉ የፐብሊክ ዲፕሎማሲና የሀብት ማሰባሰብ ተግባራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ዲፌንድ ኢትዮጵያ ከዕድሜው አንጻር ያከናወናቸው ተግባራት አበረታችመሆናቸውን አንስተው፥ በቀጣይም ለበለጠ ተልዕኮና ሃላፊነት እንደሚንቀሳቀስ ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡