Fana: At a Speed of Life!

ቀነኒሳ በቀለ የለንደን ቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ውድድርን ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን የተካሄደውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ውድድርN ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈ።

ቀነኒሳ በዛሬው እለት በብሪታኒያዋ ለንደን ከተማ የተካሄደውን የግማሽ ማራቶን ውድድር 1 ሰዓት 00 ደቂቃ 22 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል።

በዚህም ቀነኒሳ በቀለ በእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ተይዞ የነበርውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን በእጁ ማስገባት ችሏል።

ከቀነኒሳ ጋር ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ሞ ፋራህ በህመም ምክንያት ከውድድሩ ውጭ መሆኑን ቀደም ብሎ ማሳወቁ ይታወሳል።

የ5000 እና 10000 ሜትር ውድድሮች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ውድድር ሲሳተፍ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ምንጭ፦ www.bbc.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.