Fana: At a Speed of Life!

በ9 ወራት ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል-ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በዘጠኝ ወራት ባደረገው ክትትል ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፎች መያዛቸውን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በ9 ወራት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ ያከናወናቸውን ሥራዎች በሚመለከት በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አድርጓል።

የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዢነት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ ÷ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የአፈፃፀም ስልቱ ተለዋዋጭ እና በታጠቁ ኃይሎች ጭምር የሚፈጸም በመሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ እንዳደረገው ገልፀዋል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የኢንተለጀንስ ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ ÷የጉምሩክ ኮሚሽን በዘጠኝ ወራት ባደረገው ክትትል ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፎች መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮንትሮባንድ መከላከል ድንበር ቁጥጥር እና ትራንስፖርት ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮሚሽነር አይሻ ቶላ በበኩላቸው÷ ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ የነበረው ቅንጅታዊ ሥራ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ድርጊቱን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ኮሚሽነሩ መግለጻቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.