ከሳዑዲ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን በቤተ መንግስት የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳዑዲ ዓረቢያ ለተመለሱ 250 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ማምሻውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኢፍጣር አድርገዋል።
ከሳዑዲ አረቢያ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን በቤተ መንግስት በተካሄደው የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለብዙ ወራት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ እየመለሰ ሲሆን÷ ዜጎች ተጠቃልለው ወደ ሀገራቸው እስኪመለሱ ድረስ የመመለሱ ሥራ እንደሚቀጥል ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ከሳዑዲ አረቢያ ከ8 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የገቡ ሲሆን÷ በሳምንት ዘጠኝ በረራዎች መደረጋቸውም ነው የተገለፀው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የእስልምና እምነት አባቶችእና የተለያዩ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት የተሳተፉበት የኢፍጣር ዝግጅት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
በአልዓዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!