Fana: At a Speed of Life!

ለወሎ ዩኒቨርሲቲ የ18 ሚሊየን ብር የገንዘብና አይነት ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ውድመትና ዝርፊያ ለደረሰበት ወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን የ18 ሚሊየን ብር የገንዘብና አይነት ድጋፍ ተደረገለት።
ድጋፉ 10 ሚሊየን ብር ገንዘብና 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ቁሳቁስ በድምሩ 18 ሚሊየን ብር የሚገመት ሲሆን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለኮምቦልቻ ቲክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የቤተ ሙከራ ቁሳቁስ አስረክቧል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ ወሎ ዩኒቨርሲቲን መልሶ ለማቋቋም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ 13 ዩኒቨርሲቲዎችን በማስተባበር በጋራ እየተራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያው ዙር የ2 ሚሊየን የቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረጉ በተጨማሪ በሁለተኛ ዙር ድጋፍ የ8 ሚሊየን ብር የቤተ- ሙከራ ቁሳቁስ እና የመማሪያ ክፍል ወንበሮች ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
እህት ዩኒቨርሲቲዎች እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ባደረጉት ድጋፍ የመማር ማስተማር ስራው በተሳካ ሁኔታ መካሄድ መጀመሩን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.