የሶማሌ ክልል ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙባሽር ዲባድ በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ የተመራ የልኡካን ቡድን ከሶማሌ ክልል ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ሙባሽር ዲባድ ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይታቸውም በክልሉ በተከሰተው ድርቅ እና በድርቁ ሳቢያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሰጠ ባለው ምላሽ ዙሪያ መክረዋል፡፡
አቶ ሙባሽር በተከሰተው የድርቅ አደጋ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው ጃፓን በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸውን ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ ናት ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!