Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ከሕዝብ የተነሱ ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሠራ ነው – ዶክተር እዮብ ተካልኝ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ሀገሪቱ በተደረጉ ውይይቶች ከሕዝብ የተነሱ ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ፥ በቅርቡ በተደረጉ ሕዝባዊ ውይይቶች ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ ከሕዝብ በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸውን አውስተው፥ሕዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎችም በየደረጃው ለመመለስ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኑሮ ውድነት፣ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል፣ የውኃና መብራት መሰረተ ልማቶች ላይ ያሉ ክፍተቶችና አገልግሎት አሰጣጦች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ከሕዝብ ተነስተዋል ያሉት ዶክተር እዮብ፥ በተለይ ከኑሮ ውድነት ጋር በተገናኘ የተነሱ ችግሮች በፍጥነት መፈታት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።
የኑሮ ውድነቱን ችግር ለማቃለል ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠይቅ የገለጹት ሚኒስር ዴኤታው፥ ይህን ሥራ በየደረጃው ያለው አመራር ሕዝብን አስተባብሮ መሥራት አለበት ብለዋል፡፡
ዘይት ላይ የነበረውን እጥረት ለመፍታት ባልተለመደ መልኩ መንግሥት በቀጥታ ገብቶ ግዢ እንዲፈጸም መደረጉንም ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱንና በየወሩ የ50 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዢ ለመፈጸም ተወስኖ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ይህም በተወሰነ ደረጃ ከገበያ የጠፋውን የዘይት ምርት የማረጋጋት ዕድል እንዳለው መናገራቸወን ኢፒድ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.