Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰበት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት÷ በሽብር ቡድኑ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ወሎ ዩኒቨርሲቲን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲጀምር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የቤተ ሙከራ፣ የቢሮና የመማሪያ ክፍል ወንበሮች ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት፡፡ ካሁን በፊትም ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰው ድጋፋቸው እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ÷ ዩኒቨርሲቲው በሽብር ቡድኑ ከፍተኛ ጉዳ ቢደርስበትም ዩኒቨርሲቲውን እንዲደግፉ በፌደራል መንግስት የተመደቡ 13 ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች ተቋማት ባደረጉት ድጋፍ ሥራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ድጋፍ በቴክኖሎው ዘርፍ ለተማሪዎች የተሻለ ትምህርት ለመስጠት እንደሚያስችል
ጠቁመው÷ ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኮምቦልቻ ቴክኖሎኢንስቲትዩትሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶክተር መላኩ ታመነ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች በመዘረፋቸውና በመውደማቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ጫና መፈጠሩን ገልጸው÷ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው የቴክኖሎ፣ የቤተ ሙከራ፣ የቢሮና የመማሪያ ክፍል ቁሳቁስ ድጋፍ ችግሩን ያቃልላል ብለዋል፡፡
በዘሩ ከፈለኝ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.