አብርሆት ቤተ መጻሕፍት በየቀኑ ከ1 ሺህ በላይ ተገልጋዮችን እያስተናገደ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተ መጻሕፍት በየቀኑ ከ1ሺህ በላይ ተገልጋዮችን እንደሚያስተናግድ ቤተ መጻሕፍቱን ተረክቦ እያስተዳደረ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
አብርሆት ቤተ መጻሕፍት በውስጡ በተገነቡለት ዘመናዊ፣ ውብና ምቹ የአገልግሎት መሰረተ ልማቶች ምክንያት በተጠቃሚዎች ዘንድ ተወዳጅ እና በብዙ ሰዎች የሚጎበኝ ሆኗል ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም ቤተ መጻሕፍትቱ የተገነባበት ቦታ የአንድነትፓርክ፣ የወዳጅነት መናፈሻ ፓርክ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርትና ለሌሎች የተለያዩ ተቋማት ቅርብ ርቀት ላይ መገኘቱ በቀን ውስጥ ብዙ ተጠቃሚዎች እንዲጎበኙት አስችሏል ተብሏል፡፡
አብርሆት ቤተ- መጻሕፍት አሁን ላይ የተለያዩ የጥናት ወረቀቶችን በሚያዘጋጁ የከፍተኛ ትምህርት ባለሙያዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር እና ሌሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የከተማው ነዋሪዎች እየጎበኙትና አገልግሎት እያገኙበት መሆኑንም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
ቤተ መጽሀፍቱን ተረክቦ እያስተዳደረ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ በየቀኑ ከ1 ሺህ በላይ ተገልጋዮች እየጎበኙት ይገኛል፡፡
ቤተ መጻሕፍቱ በአንድ ጊዜ እስከ 2 ሺህ 500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን÷ ከኢ-ላይብራሪ አገልግሎት በተጨማሪ ከ1 ነጥበብ 4 ሚሊየን በላይ የተለያየ ይዘት ያላቸው መጽሀትፍን በውስጡ ያካተተ ነው፡፡
አብርሆት ቤተ መጻሕፍት የከተማውን ነዋሪ ህብረተሰብ የንባብ ባህል በማጎልበት ጠቃሚ የሆኑ ቁም ነገሮች የሚያገኙበት ስፍራ እንዲሆን ታስቦ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ የተገነባ የመዲናዋ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!