ህወሓት በወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት የጅምላ ግድያና የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጥናት አመላከተ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርስቲ በወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር ያጠናውን የጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡
21 አባላት ያሉት የጥናት ቡድኑ ባደረገው ጥናት አሸባሪው ህወሓት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የፈጸማቸውን ጭፍጨፋዎች ለማጥናት እና ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ሰርቷል።
በጥናቱም አሸባሪው ህወሓት በወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን አመላክቷል።
የሽብር ቡድኑ ተቋማዊ ማንነትን ለመቀየር ሰርቷል፣ የትምህርት ቤት እና ሆስፒታል ስያሜዎች ትግርኛ ቋንቋ ብቻ ማድረጉም በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡
ቡድኑ የማፈናቀል እና በሃይል አካባቢውን ለመቆጣጠር ሰርቷል ያለው ዩኒቨርሲቲው ፥ይህን ተክትሎም በአካባቢው የተለያዩ ጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን አስታውቋል።
በእስካሁኑ ጥናት የጅምላ መቃብሮች የተገኙት በስውር ቦታዎች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፥አንዳንዶቹ የእርሻ ቦታዎች እንዲሆኑ የተደረጉ ናቸው ተብሏል።
ማህበረሰቡ መቃብሮቹን በግልጽ እንደሚያውቁ እና እነማን እንደተቀበሩ መረጃ እንዳላቸውም በጥናቱ ተመላክቷል።
ከዚህ ባለፈም ማጎሪያ ቤቶችና ዋሻዎች መገኘታቸውን እና በወልቃይት ጠገዴ እና በጠለምት አካባቢዎች በሚገኙ አሰቃቂ እስር ቤቶች ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎች መፈጸማቸው ተገልጿል፡፡
በለይኩን ዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!