Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ አቅርቦት እና ስርጭትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመደገፍ ዘርፉን ማዘመን እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ አቅርቦት እና ስርጭትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ መቆጣጠርና ማስተዳደር በሚቻለበት ሁኔታ ላይ “ዲጂታል ኤሌክትሪክ እና ኢነርጂ” በሚል የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
 
በውይይቱ÷ ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን እያስፋፋች ቢሆንም አቅርቦቱ፣ ስርጭቱና ቁጥጥሩ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አለመደገፉ ተመላክቷል፡፡
 
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ ÷ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን በዲጂታል አሰራሮች በመደገፍና በማሻሻል የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
 
ያለ ኤሌክትሪክ አቅርቦት የኢኮኖሚ ልማት ሊታሰብ አይችልም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው÷ ታማኝና ደንበኛ ተኮር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል የኃይል አስተዳደር ለመዘርጋት ይሰራል ብለዋል፡፡
 
በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ውስጥ 21 ከመቶ የኃይል ብክነት እንደሚከሰት የተገለፀ ሲሆን÷ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና ዘመናዊ የኃይል አስተዳደር እንዲኖር የዲጂታል አሠራር መዘርጋት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
 
በዲጂታል አሠራር የተደገፈ የኃይል አቅርቦት፣ ብልሽት ከማጋጠሙ በፊት ቁጥጥር ለማድረግ፣ ጥገና ሲያስፈልግ አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት እና ብክነትን ለመቆጣጠር ይረዳል ተብሏል፡፡
 
በውይይቱ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.