Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል እስካሁን የተካሄዱ የምርመራና የመልሶ ማቋቋም ስራን ገመገመ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችን አስመልክቶ እስካሁን የተካሄዱ የምርመራና የመልሶ ማቋቋም ስራዎችን ገምግሟል፡፡
ግብረ ሀይሉ በስሩ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች እየሰሯቸው ያሉ ስራዎችን እና ስራዎቹ ያሉበትን ደረጃ ነው የገመገመው፡፡
የሰሜኑን ግጭት ተከትሎ በሶስቱም ክልሎች ማለትም በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንዲሁም የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ተመልክቷል።
በተለይም ስራውን በጀመረባቸው በአማራና አፋር ክልሎች የተፈፀሙ ወንጀሎችን የማጣራትና ወንጀለኞቹን ለፍርድ የማቅረብ ሂደት ያለበት ደረጃ በዝርዝር ታይቷል።
እስካሁን ወንጀሎች እና ወንጀሎቹ በማንና እንዴት ተፈፀሙ ከሚለው ጋር በተገናኘ በርካታ የአይን ምስክሮችን ለማነጋገር መቻሉን እና በቂ ማስረጃ በማሰባሰብ ወንጀለኞች ላይ ክስ ለመመስረት ሂደት መጀመሩ ተገልጿል።
በሂደቱ የተገኙ ስኬቶችና እጥረቶችም ተዳሰዋል።
የተመድ የሰብዓዊ መብት ተቋም እና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባደረጉት የጋራ ምርመራ የተሰጡትን ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር ኢትየጵያ ተግባራዊ አንቅስቃሴ በማድረግ የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል መቋቋሙ ይታወቃል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.