አምባሳደር መለስ ዓለም የላሙ ፕሮጄክት ለኢትዮጵያ ባለው ጠቀሜታ ላይ ከዋና ስራ አስፈፃሚው ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ከላሙ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ስቴፈን ኢኩዋን ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።
አምባሳደር መለስ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን አማካይነት የመሰረተ ልማት ትስስር ለመፍጠር እየተካሄደ ያለው የላሙ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሦስቱን አገራት በኢኮኖሚ በማስተሳሰር ረገድ ባለው ከፍተኛ ሚና ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል።
በተለይም የላሙ ፕሮጄክት ለአገራችን የወደብ አማራጭ በመሆን ከሚኖረው ጠቀሜታ አኳያ ፕሮጀክቱ እንዲፋጠን በሦስቱ አገራት በኩል ያላሰለሰ ጥረት መደረግ እንዳለበት ነው አምባሳደሩ የተናገሩት።
አገራችንም ለፕሮጀክቱ መሳካት ያላትን ፍላጎት እና ዝግጁነት አምባሳደሩ ጠቁመዋል።
የላሙ ፕሮጄክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ በበኩላቸው፥ የላሙ ፕሮጀክት እንዲፋጠን ሦስቱም አገራት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው እና ኢትዮጵያም በዚህ ረገድ ያላትን ዝግጁነት እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።
አምባሳደሩ እና ዋና ሥራ አስፈፃሚው የፕሮጀክቱን ትግበራ ለማፋጠን የተጀመሩ ውይይቶች እንዲቀጥሉ በጋራ እንደሚሰሩ መስማማታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!