Fana: At a Speed of Life!

ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ከ 20 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልልች በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል በዓይነት ብቻ 20 ሚሊየን 704 ሺህ 292 ብር ግምት ያለው ቁሳቁስ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አስታወቀ፡፡
“200 ለእናቴ አንድ ዕቃ ለአንድ ተፈናቃይ” በሚል መሪ ሀሳብ በመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በተጀመረው ንቅናቄ÷ በዓይነት ብቻ 20 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ቁሳቁስ ለመሰብሰብ ታቅዶ ነው 20 ሚሊየን 704 ሺህ 292 ብር ግምት ያለው ቁሳቁስ የተሰበሰበው፡፡ ይህም የዕቅዱን 103 ከመቶ ማሳካት እንደተቻለ ነው የተመላከተው፡፡
የተሰበሰበው ከ3 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ብር በተከፈተው የጋራ አካውንት ገቢ መደረጉም ተገልጿል፡፡
የተሰበሰበው ድጋፍ አልባሳት፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ ምግብ ነክ የሆኑ እና የቤት ውስጥ የማብሰያ እንዲሁም የመመገቢያ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው፡፡
የተሰበሰበው የቁሳቁስ ድጋፍም በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ እና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚበረከት ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ወደ አማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን ይላካል ተብሏል፡፡
በአዲሱ ሙሉነህ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.