Fana: At a Speed of Life!

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የክትትል ስራዎች ይጠናከራሉ – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይሠራል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙ ሼዶች፣ የወጣቶች ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የባህል ማዕከል ማስፋፊያዎች እና የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት÷ ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የልማት ስራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለዚህም የክልሉ መንግስት ግንባታዎቹ በአፋጣኝ እንዲጠናቀቁ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡
የግንባታዎቹ በፍጥነት መጠናቀቅ የስራ እድልን ከመፍጠር ባሻገር ወጣቱ አልባሌ ስፍራ እንዳይውል ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ጠቁመው÷ ግንባታቸው በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ ለጉዳት እየተዳረጉ ያሉ ፕሮጀክቶችንም ከጉዳት እንደሚታደግ ማብራራታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.