Fana: At a Speed of Life!

“ሂውማን ብሪጅ” የተሠኘ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የሕክምና ግብዓት ለደብረብርሃን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ

መቀመጫውን ስዊድን ያደረገው “ሂውማን ብሪጅ” የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ለደብረብርሃን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የሕክምና ግብአት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ለሆስፒታሉ ያስረከቡት የ”ሂውማን ብሪጅ” የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር አዳሙ አንለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እደተናገሩት ድርጅታቸውን ደራሽ የዳያስፖራ ፈንድ በጠየቀው መሠረት የሆስፒታሉን የአልጋ ችግር ሙሉ በሙሉ የሚፈቱ እና ለታካሚዎች ምቹ የሆኑ 157 ሀይድሮሊክ ዘመናዊ አልጋዎችን ከነፍራሻቸው እንዲሁም ለታካሚ መንቀሳቀሻ የሚሆኑ 20ዊልቸሮችን ለሆስፒታሉ ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው ገለጹት፡፡

የ“ሂውማን ብሪጅ “ ዳይሬክተር ÷ በቀጣይም በአማራክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ስድሥት ሆስፒታሎች ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ ግብአቱን ወደሀገር ውስጥ እያስገባን ነው ብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተወካይ ሥራ ስኪያጅ አቶ ፅግሸት ነጋሽ በበኩላቸው ÷ በሆስፒታላቸው ያሉት የታካሚዎች አልጋ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠታቸው ያረጁና ለታካሚዎችም ምቹ ያልነበሩ በመሆናቸው ለታካሚዎችም ሆነ ለባለሙያው አገልግሎት ለመሰጠት እንቸገር ነበር ብለዋል።

ይህን የሆስፒታሉን ችግር ያዩ ዳያስፖራ ሐኪሞች” ሂውማን ብሪጅ”ን በማስተባበር ያደረጉልን ድጋፍ በዘርፉ ያለውን ችግር የቀረፈና ሆስፒታሉ ታካሚዎችን በተሻለ መንገድ እዲያገለግል ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

ድጋፋን ከጂቡቲ ወደብ ወደሆስፒታሉ ለማድረስ የወጣውን ከ630ሺህ ብር በላይ ወጪ በጋዜጠኛ ደረጀ ሐብተወልድ አስተባባሪነት መሸፈኑን አንስተዋል፡፡

አቶ ፅግሸት ነጋሽ ÷ ድጋፉን ላደረጉና ላስተባበሩ ካላት በተገልጋዮችና በሆስፒታሉ ስም ምስጋናም አቅርበዋል።

በአበበ የሸዋልዑል

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.