Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ ስለ ኮሮና ቫይረስ የሚሰራጩ አሳሳች ማስታወቂያዎችን ሊያግድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በገጹ ላይ የሚወጡ አሳሳች ማስታወቂያዎችን እንደሚያግድ አስታወቀ።

ኩባንያው ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ ወይም ሊከላከሉ ይችላሉ የተባሉ ምርቶች ማስታወቂያዎችን እንደሚያግድ አስታውቋል።

የኮሮና ቫይረስን ስም በመጥቀስ በገጹ ላይ የሚለጠፉ የምርትና አገልግሎት ማስታወቂያዎችን እንደሚያግድ ገልጿል።

ቫይረሱን ለመከላከልና ከቫይረሱ ነጻ ለመሆን ይረዳሉ በሚል የሚለቀቁ ማስታወቂያዎች የኩባንያው ኢላማወች ናቸው።

ለአብነትም “የፊት ጭምብሎች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል 100% ዋስትና አላቸው” የሚል ይዘት ያላቸውን ማስታወቂያዎች እንደማይፈቅድም ነው ያስታወቀው።

የአሁኑ የኩባንያው እርምጃ በገጹ ላይ ጽንፍ የያዙ ሃሳቦችና ሃሰተኛ መረጃዎችን እየተከላከለ አይደለም በሚል የቀረበበትን ውንጀላ ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.