Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሀርጌሳ ገበያ ማዕከል ላይ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በደረሰው ውድመት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ከተማ በተነሳው የእሳት አደጋ በተፈጠረው ሰብዓዊ እና የንብረት ውድመት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት፥ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከሶማሊላንድ ህዝብ ጎን መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

“በተከበረው የረመዳን ወር ላይ ባለንበት በዚህ ወቅት እነዚያን ኪሳራዎች ወደ ትርፍ እንዲለውጥ ከአላህ እንጠብቃለን፥ አላህ የኛ ነው፤ ወደርሱም ተመላሾች ነን” ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.