የኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ቡድን ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋገጠ።
በዛሬው የምድብ “ሐ” መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ቡድን ደቡብ ፖሊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ መድን ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም በምድብ “ሀ” የተደለደለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉ ይታወሳል።