Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ባንክ በሶማሌ ክልል በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች 15 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ባንክ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል የ15 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የአዋሽ ባንክ የምስራቅ ኢትዮጵያ ዲስትሪክት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወጋየሁ ተሾመና የአዋሽ ባንክ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ አመራሮች በጅግጅጋ ከተማ ተገኝተው ለሶማሌ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ አስረክበዋል።

አዋሽ ባንክ ከማህበረሰቡ ጋር በቅርበት እንደ መስራቱ መጠን የክልሉን ህዝብ ችግር እንደራሱ ችግርና ጉዳት ተረድቶ ድጋፍ ማድረጉን የባንኩ ዲስትሪክት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወጋየሁ ተሾመ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ተቋማት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን የመወጣት ግዴታ አለባቸው ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ ምክትል ቢሮ ሐላፊ አቶ ሳዲቅ አብዲቃድር በበኩላቸው÷ በድርቁ ምላሽ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ የድርቅ ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋምና ወደ ቀያቸው በመመለስ ስራ ላይ ሁሉም ተቋም የራሱን ድርሻ ሊወጣና ሊደግፍ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በድጋፍ ማስረከብ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ገለልተኛ የድርቅ ምላሽ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴና የተለያዩ የአገር ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን÷ ባንኩ ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.