Fana: At a Speed of Life!

ከነገ ጀምሮ ለነባር እና ለአዳዲስ የሃይማኖት ቴሌቪዥን አመልካቾች ፈቃድ መስጠት ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጋቢት 23 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለነባር እና ለአዳዲስ የሃይማኖት ቴሌቪዥን አመልካቾች ፈቃድ መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገለጸ።

ባለስልጣኑ በሃይማኖት ብሮድካስት ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ውይይት እያደረገ ነው።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ÷ቀደም ሲል በነበሩት የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ እና ህጎች መሰረት የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት ብሮድካስት እንዳያቋቁሙ ህጋዊ እውቅና እና ፈቃድ እንዳያገኙ ተከልክለው መቆየታቸውን ንስተዋል፡፡

በህብረተሰቡ ዘንድ የሃይማኖት መርሃ ግብር በቴሌቪዥን ለመከታተል ከነበረው ፍላጎት ጋር በተያያዘ ሃገራዊ ለውጡን ተከትሎ የሃይማኖት ብሮድካስተሮች በህግ ዕውቅና እንዲያገኙ፤ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲውም ሆነ የአዋጅ ማሻሻያ በመደረጉ ባለስልጣኑ ፈቃድ አውጥተው እንዲንቀሳቀሱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋልም ነው ያሉት ።

በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሰረትም ከመጋቢት 23 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለነባርም ሆነ ለአዳዲስ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ፈቃድ አመልካቾች ፈቃድ መስጠት የሚጀምር መሆኑን ተናግረዋል።

በተደረገው ጥናት መሰረት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ50 በላይ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በስርጭት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፥ ጣቢያዎቹ ሃይማኖታዊ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ለተከታዮቻቸው አማራጭ የመገናኛ ዘዴ በመሆን እያገለገሉ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

በአንጻሩ ጥቂት የሚባሉ በሃላፊነት ስሜት እና በጥንቃቄ የማይንቀሳቀሱ የሃይማኖት ሚዲያዎች በመኖራቸው በሚያሰራጯቸው መረጃዎች ከህብረተሰቡ የሚደርሱ ቅሬታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ እንደሚገኙም አንስተዋል።

ከነዚህ ቅሬታዎች ውስጥም ከሕግ፣ ከሞራል፣ ከጤና ጋር የሚቃረኑ ንግግሮችን የማሰራጨት እና ሌሎች ሃይማኖቶችን የመንቀፍ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

በመሆኑም የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ለሃገር አንድነት፣ ለህዝብ መፈቃቀር ፣ አብሮነት፣ መረዳዳት፣ ሰላም እና መሰል በጎ ሃይማንታዊ ዕሴቶችን በማጠናከር የበኩላቸውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምንይችል አዘዘው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.