Fana: At a Speed of Life!

በፍትህ ሚኒስቴርና በክልል ፍትህ ቢሮዎች መካከል በህግ እና ፍትህ ማሻሻያ ዙሪያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፍትህ ሚኒስቴር እና በክልል ፍትህ ቢሮዎች መካከል በህግ እና ፍትህ ማሻሻያ ዙሪያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።

በውይይቱ የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዴዮን ጢሞቴዎስ፣ የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለም አንተ አግደው፣ የሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የፍትህ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ተመራማሪዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ።

ለሶስት ቀናት ሲቃሄድ ቆይቶ ዛሬ በተጠናቀቀው የምክክር መድረክ የተሞክሮ ልውውጥ ተካሂዷል።

የህግ አካላት ኃላፊነት፣ የህግ ማርቀቅ እና የማረም ስራዎች ሂደት፣ ህጎችን የማጠቃለል የህግ ዘርፉን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎች እና መሰል ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል።

የፌደራል ህጎችን ተፈጻሚነት የተመለከቱ እና መሰል የፍትህ ዘርፉን የተመለከቱ ጉዳዮች በአቶ አለምአንተ አግደው የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ቀርበው የተሞክሮ ልውውጥ ተካሂዶባቸዋል።

ባለፉት ዓመታት በተደረጉ የፍትህ ማሻሻያዎች የተገኙ ውጤቶች እና የታዩ ድክመቶች መገምገማቸውን ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናግረዋል፡፡

በግምገማው በፌዴራል ደረጃ የወጡ ህጎችን ለተናበበ እና ለቅንጅታዊ አሰራር በማዋል በኩል ክፍተቶች መታየታቸውን አንስተዋል፡፡ አሁን በባህር ዳር የተካሄደው የምክክር መድረክም የታዩ ክፍተቶችን ለማረም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.