Fana: At a Speed of Life!

ሴኔጋል እና ካሜሮን ለ2022 ዓለም ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴኔጋል እና ካሜሮን ለ2022 ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ተወካይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ሴኔጋል በፍፃሜው ያገኘቻትን ግብፅን በድጋሚ በመለያ ምት በማሸነፍ ለኳታሩ 2022 ዓለም ዋንጫ ጨዋታ ማለፏን አረጋግጣለች።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሴኔጋል ካይሮ ላይ በግብፅ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መሸነፏ ይታወሳል።
ትላንት በዳካር በተካሄደው የመልስ ጨዋታ ግብጻዊው ተከላካይ ሃምዲ ፋቲ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ጎል በመደበኛው እና በተጨማሪው 30 ደቂቃ 1 ለ 1 በሆነ ድምር ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል፡፡
ለዓለም ዋንጫ የሚያልፈውን ቡድን ለመለየት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት ሴኔጋል ግብፅን 3 ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች፡፡
በዚህም ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በዓለም ዋንጫው መድረክ ላይ የሚታይ ሲሆን፥ የክለብ አጋሩ ሞሃመድ ሳላህ በዓለም ዋንጫው መሳተፍ የሚችልበት እድል መክኗል፡፡
በሌላ ጨዋታ ካሜሮን በሜዳዋ የደረሰባትን የ1ለ 0 ውጤት በመቀልበስ አልጄሪያን በሜዳዋ 2 ለ 1 በማሸነፍ ከሜዳ ውጭ ብዙ ያገባ በሚለው የፊፋ ህግ ለዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች፡፡
ኢሪክ ሞቲንግ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ለከሜሮን ጎል ማስቆጠር ሲችል ካርል ቶኮ ኢካምቤ ባለቀ ደቂቃ ያሰቆጠራት ጎል የካሜሮን የዓለም ዋንጫ እጣ ፋንታ ወስናለች፡፡
በሌላ ጨዋታ ቱኒዚያ ማሊን፣ ሞሮኮ ዴሞክራቲክ ኮንጎን እንዲሁም ጋና ናይጄሪያን በመርታት ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ እንዳለፉ ማረጋገጣቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.