ዘመን ባንክ የማስተር ካርድ የክፍያ ስርዓት መተግበር የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘመን ባንክ ኤም ፒ ጂ ኤስ የተባለ የማስተር ካርድ ስርዓትን በማስጀመር ክፍያዎችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ቴክኖሎጂን አስተዋውቋል።
ይህንን ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀው ከማስተር ካርድ ጋር በመሆን ነው።
ይህ የክፍያ ስርዓትም ለአየር መንገድ እንዲሁም ለሆቴሎች ቅድሚያ አገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ነው ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የኦንላየን ግብይቶችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ነው።
ይህ የክፍያ ስርዓትም በኢትዮጵያ ብርም መገበያየት የሚያስችልና የቀጥታ ክፍያ ንክኪን የሚቀንስ ነው።
ኢኮሜርስ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣ ከመሆኑ አንጻር እንዲህ አይነት ቴክኖሎጂ ግብይቱን በአንድ ቦታ በመጨረስ እንዲቀላጠፍ ያደርጋል።
በዘመን በየነ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!