በሩሲያ ላይ እየተጣሉ ያሉ ማዕቀቦች አውሮፓን ዋጋ እያስከፈሉ ነው – የግሪኩ ጠቅላይ ሚኒስትር
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ላይ እየተጣሉ ያሉ ተደጋጋሚ ማዕቀቦች በአውሮፓ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ዋጋ እያስከፈሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲሉ የግሪኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪርያቆስ ሚትሶታኪስ አስጠነቀቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሲ ኤን ኤን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳሉት፥ በሩሲያ ላይ የተጣሉ ተደጋጋሚ ማዕቀቦች በአውሮፓ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ዋጋ እያስከፈሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
እንደ አውሮፓ የእድገት ትንበያችንንም እንደገና መገምገም አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በጦርነቱ ምክንያት በአውሮፓ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ሊገጥም እንደሚችል እና የኃይል አቅርቦት ችግርም ሌላው የአህጉሪቱ ስጋት እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
አውሮፓ እንደ አህጉር ዩክሬንን ለመደገፍ ብዙ ርቀት እንደሄደች የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሩሲያ ላይ ተደጋጋሚ ማዕቀቦች መጣሉ ጦርነቱን በማባባስ የዩክሬን ዜጎችን ለባሰ ውጥረት እና ለከፋ ችግር እንደሚዳርግ ማሰብ ይገባልም ማለታቸውን የቱርኩ የዜና አውታር (አናዶሉ) ዘግቧል፡፡
አንድ ወር ባስቆጠረው የሩስያ -ዩክሬን ግጭት የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካ ፣ብሪታንያ እና ሌሎች ሀገራት በሞስኮ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን መጣላቸው ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!