Fana: At a Speed of Life!

ከ21 በላይ የታሸገ ውኃ አምራች ፋብሪካዎች ስራ አቆሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ21 በላይ የሚሆኑ የታሸገ ውኃ አምራች ፋብሪካዎች ስራ ማቆማቸው ተገለጸ።

ውሃ አምራች ፋብሪካዎች ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፣ ጉሙሩክ ኮሚሽን እና አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

በመላ ሀገሪቱ 134 የሚሆኑ የታሸገ ውኃ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በተለያዩ ምክንያቶች 21 የሚሆኑ ፋብሪካዎች ስራ ማቆማቸው ተገልጿል።

የቀሩት ፋብሪካዎችም በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ እንዳልሆነ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

የጥሬ ዕቃ ዋጋ መጨመር እና በሽያጭ ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝን አለመጠቀም፣ የጉምሩክ ቀረጥ በኢንቮይስ መሰረት አለመስተናገድ፣ የታሸገ ውኃ መጠጥን እንደ ቅንጦት በመውሰድ አላስፈላጊ የሆነ የኤክሳይስ ታክስ ጫና መፍጠር እና ለአምራቹ የውጭ ምንዛሪ ቅድሚያ አለመስጠት ለስራቸው ተግዳሮት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ቸርቻሪው አምራቹ ከጨመረበት ዋጋ ዉጪ ከሶስት እጥፍ በላይ ዋጋ በመጨመር ለኑሮ መወደድ ዋና ተዋናይ እየሆነ ነው ሲሉም አምራቾቹ ቅሬታ አቅርበዋል።

በማህሌት ተክለብርሃን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.