የተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫ የማመልከቻ ቀን መራዘሙን ሚኒስቴሩ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመመደብ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫ የማመልከቻ ቀን መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸውን ይታወሳል።
ስለሆነም ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቀው÷ የሚከተሉትን መረጃዎች እንዲያመለክቱ ጠይቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et በመግባት እንዲያስተካክሉ አሳስቧል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ አሳስቦ በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማያስናግድ መሆኑንም ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!