በህልውና ዘመቻው የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እዉቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህልውና ዘመቻው የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሠራዊት አባላት፣ ሲቪል ሠራተኞችና ክፍሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ጤና ዋና መምሪያ እውቅና ተሰጠ።
በምስጋና እና የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በክብር እንግድነት መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በአገር የማዳንና የህልውና ዘመቻው ወቅት የጤና ባለሙያዎች ያበረከቱት ሙያዊ አስተዋጽኦ በታሪክ ሲታወስ የሚኖር ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡
በአገር የማዳንና የህልውና ዘመቻው ወቅት የጤና ባለሙያዎች ያበረከቱት ሙያዊ አስተዋጽኦ በታሪክ ሲታወስ የሚኖር መሆኑን ገልጸዋል።
ከጤና ሚኒስቴር፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከሌሎች ጋር በመቀናጀት በዘመቻው ወቅት የተሻለ የጤና አገልግሎት መሰጠቱንም ተናግረዋል።
በቀጣይ የመከላከያ ሆስፒታሎችን ለማብዛት፣ ሰራዊቱ ጠንካራ የጤና አገልግሎት እንዲኖረውና የጤና ባለሙያዎች አቅም ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የመከላከያ የጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ጥጋቡ ይልማ÷ ሰራዊቱ ተልዕኮውን በሚፈለገው መንገድ እንዲወጣ ድጋፍ ሰጪዎች የራሳቸውን የላቀ ሚና መወጣታቸውን ገልጸዋል።
ዘመናዊ የጤና አገልግሎት በብቃት ለመስጠት የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው በጤና መምሪያው ስር የሚገኙ የጤና ተቋማት በቁሳቁስ እና በሰው ኃይል የማጠናከር ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።
የማዕረግ የዕድገትና እውቅና የተሰጣቸው ሰራተኞች በበኩላቸው÷ የተሰጣቸው እውቅና ለበለጠ ስራ እንደሚያነሳሳቸው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!