Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የ2022ቱን “ዓለም አቀፍ የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤን” ልታስተናግድ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የ2022ቱን “ዓለም አቀፍ የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤን” እንደምታስተናግድ ተገለጸ፡፡

ጉባዔውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን እና ኤክስቴሽያ በትብብር የሚያዘጋጁት ነው።

በጉባዔው ከ30 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ300 እስከ 500 የሚደርሱ ሚኒስትሮች፣ የቴክኖሎጂ ድርጅት ኃላፊዎች እና ከፍተኛ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ የኢኖቬሽን ዲጂታል አፍሪካ ጉባዔ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መወሰኑ ኢትዮጵያ ተመራጭ እየሆነች መምጣቷን ማሳያ ነው ብለዋል።

ጉባዔውን ለማስተናገድ የኢትዮጵያን ዝግጁነት ያረጋገጡት ሚኒስትሩ ፥ ኢትዮጵያ ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አጋዥ የሆኑ የመፍትሄ ሃሳቦችን የምታገኝበት እንደሚሆን ተናግረዋል።

ጉባዔው ግንቦት 3 እና 4/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ፥ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የዲጂታል ቴክኖሎጂ የመፍትሄ ሃሳቦች የሚቀርቡበት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.