Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር ሃይል  አጠቃላይ ዝግጁነትና አሁን ያለበት ቁመና አስደስቶናል – ታዋቂ ግለሰቦች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ሃይል አጠቃላይ ዝግጁነትና አሁን ያለበት ቁመና አስደስቶናል፤ ኩራትም ተሰምቶናል ሲሉ በቢሾፍቱ አየር ሃይል ጉብኝት ያደረጉ የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦች ገለጹ።

የኢትዮጵያ የምንጊዜም ጀግናዋን አትሌት ደራርቱ ቱሉ ጨምሮ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች በቢሾፍቱ የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው በተመለከቱት የኢትዮጵያ አየር ሃይል አጠቃላይ ዝግጁነትና ያለበት ቁመና መደሰታቸውን እና መኩራታቸውን ተናግረዋል።

“በኢትዮጵያ አየር ሃይል በነበረኝ ጉብኝት በተመለከትኩት ሁሉ ደስታና ኩራት ተሰምቶኛል” ስትል ጀግናዋ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ገልፃለች።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከዘመኑ ጋር ዘምኖ የአገር አለኝታ እንዲሆን ላደረጉ ሁሉ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ይገባቸዋልም ብላለች።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ለመጀመሪያ ጊዜ መጎብኘቱን ገልፆ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ምን ጊዜም የአገር ኩራት መሆኑን በተግባር ተመልክቻለሁ ብሏል።

ከዚህ በፊት ለመግባት ይቅርና በውጭ እንኳን በአይን ለማየት ይከለከል የነበረን ቦታ ገብቶ በማየቱ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረለት መናገሩን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይልን የመሰለ ዘመናዊ ተቋም ለህዝብ ክፍት ሆኖ ማየት መቻል የእኔነት ስሜት ከመፍጠሩ በላይ ደስታና ኩራቱ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ዮናስ ዘውዴ በጉብኝታቸው አየር ሃይል የነገይቷን ኢትዮጵያ አመላካችና አለኝታ መሆኑን በቅጡ ተረድቻለሁ ብለዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተገኘው አርቲስት አብራር አብዶ በበኩሉ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከዚህ ቀደም ከሚያውቀው በእጅጉ የተደራጀና የዘመነ ሆኖ በማግኘቱ መደነቁን ገልጿል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.