Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ፡፡
የአምባሳደሯ ጉብኝት አየር መንገዱ በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ቦይንግ 777-8 የጭነት አውሮፕላኖችን እንደሚገዛ ማስታወቃቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ስምምነቱ አየር መንገዱን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው የጭነት አገልግሎት ፍላጎት ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሲሆን፥ እያስመዘገበ የሚገኘውን ዕድገትም ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ “በአፍሪካ አቪየሽን መስክ ቀዳሚ አየር መንገድ እንደመሆናችን መጠን ይህንን አዲስ፣ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
ይህ አዲሱ ቦይንግ 777-8F የጭነት አውሮፕላን እያደገ የመጣውን የአየር መንገዱን የጭነት አገልግሎት በማስፋፋት አሁን ያሉትን 66 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳዋል” ማለታቸውን ከአሜሪካ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.