Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋልያዎቹ ባለባቸው ጨዋታ ምክንያት ለሦስተኛ ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋልያዎቹ ከኮሞሮስ በሚያደርጉት ጨዋታ ምክንያት ለሦስተኛ ጊዜ መራዘሙ ተገልጿል፡፡
የመጀመሪያ ዙር የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየርሊግ መጠናቀቁን ተከትሎ የቀጣይ የጨዋታ መርሃ ግብሩ ከ15 ቀን ዕረፍት በኋላ እንደሚቀጥል የአክሲዮን ማህበሩ ቢያስታውቅም ውድድሩ አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ መራዘሙ ታውቋል ።
ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኮሞሮስ ጋር ላለበት የወዳጅነት ጨዋታ መሆኑ ነው የተገለፀው።
በዚህም መሠረት ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ኮሞሮስ ተጉዞ የወዳጅነት ጨዋታውን መጋቢት 16 ቀን የሚያደርግ ሲሆን÷ ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታውን አድርጎ መጋቢት 17 ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ የሁለተኛ ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መጋቢት 21 ቀን በአዳማ ይካሄዳሉ ተብሏል።
በወጣው የጨዋታ መርሐ ግብር መሠረት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለስድስት ሳምንታት እንደሚደረግ ከቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.