የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የጀርመኑ ጂ አይ ዜድ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ የልማት ተቋም ጂ አይ ዜድ ጋር የ10 ሚሊየን ብር ስምምነት ተፈራርሟል።
ስምምነቱ የካፍ የልህቀት ማዕከል የመጫወቻ እና ልምምድ ሜዳን ደረጃ ለማሻሻል እንዲሁም አዲስ ተጨማሪ ሜዳ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።
በስምምነቱ መሠረት ጂ አይ ዜድ በካፍ የልህቀት ማዕከል የሚገኘውን የመጫወቻ ሜዳ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የመልሶ ግንባታ ሥራ የሚያከናውን ሲሆን፥ አንድ ተጨማሪ አዲስ ሜዳ ደግሞ የሚገነባ ይሆናል።
ከመልሶ እና አዲስ ግንባታው በተጨማሪ ለጥገና እና እንክብካቤ ሠራተኞች የሚሰጠው ስልጠናም የስምምነቱ አካል ነው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!