Fana: At a Speed of Life!

በህዝቦች መካከል ልዩነት በመፍጠር የሰላም እጦት እንዲከሰት የሚጥሩ ኃይሎችን እንደሚታገሉ – የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በሰገን ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሔደ ነው ፡፡

በኮንፈረንሱ ከኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የአካባቢያችንን ሰላም በማስጠበቅ በሀገሪቱ የተጀመረውን ልማት እናስቀጥላለን ብለዋል።

በህዝቦች መካከል ልዩነት በመፍጠር የሰላም እጦት እንዲከሰት የሚጥሩ ኃላሎችን አምርረን በመታገል ለጋራ እድገት በአንድነት እንሰራለን ብለዋል።

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ፥ ባለፉት 27 ዓመታት የነበረው ስርዓት ከአንድነት ይልቅ ልዩነታችን ላይ እንድናተኩር አድርጓል ብለዋል።

የሰላም ተምሳሌት የሆነውን የኮንሶ ህዝብ ለመከፋፈል የሚጥሩ ሀይሎችን ሴራ በማጋለጥ አካባቢው ሰላማዊ እንዲሆን ሲተጉ ለነበሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የዞኑ ህዝብ ችግሮችን በጽናት በመሻገር የሰላም እሴት ባለቤት እንዲሁም ለአሁኑ ዘመናዊ የአስተዳደር ስርዓት ተምሳሌት መሆኑን አንስተውም፥ የተጀመረው የሰላም እሴት ግንባታ እንዲጠናከር የክልሉ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም ጠቁመዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው፥ ህብረተሰቡ በተፈጥሮ የተቸረውን ጥበብ በመጠቀም ለፍቅር በመሸነፍ ለእውነት መኖር እንደሚቻል ማሳየቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.