Fana: At a Speed of Life!

ከበይነ መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች ምንነት እና የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ምንድን ነው?

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ወቅት ከበይነ መረብ ጋር የተቆራኙ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት እየጨመረ ይገኛል፡፡
 
ከበይነ መረብ የተቆራኙ ቁሶች (internet of things) በዋናነት ሴንሰሮች እና ሶፍትዌሮች የተካተቱባቸው የቁሶች ትስስር ማለት ሲሆን÷ በበይነመረብ አማካኝነት ከሌሎች መሳሪያዎች እና ስርዓቶች ጋር ለመገናኘት እና መረጃን ለመለዋወጥ የሚያስችሉና በዋናነት የገመድ አልባ አዉታረ-መረብን የሚጠቀሙ ቴክኖሎጂዎች ናቸው።
 
እነዚህ መሳሪያዎች ከተራ የቤት እቃዎች(እንደ ስማርት ፍሪጆች፣ ቴቪ፣ ስፒከሮች) እስከ ውስብስብ የኢንዱስትሪ መሳሪያዎች (እንደ ጤና፣ ግንባታ፣ ኢነርጂ፣ በእርሻ እንዲሁም በትራንስፖርት) የሚደርሱ ሲሆን÷ የሰዎችን፣ የስርዓቶችን እንዲሁም የቁሶች እንከን የለሽ ግንኙነት መፍጠር የሚያስችሉ ናቸው።
 
ከበይነመረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ፡-
ከበይነመረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች ስራን ለማቀላጠፍና ህይወትን ቀላል ለማድረግ ትልቅ ሚና ቢኖራቸውም በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከሚሰጡት ጥቅም በተቃራኒ ለደህንነት ስጋትም ተጋላጭ ናቸው፡፡
 
በቁሶቹ ላይ የሳይበር ጥቃት እንዲደርስ በብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በአብዛኛው ግን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሲከሰቱ ይስተዋላል።
 
• የደህንነት ክፍተት እና የግላዊነት ጉድለት
 
• ቁሶቹ የተካተቱባቸው የዌብ ሰርቨሮች ክፍተት መኖር
 
• የባለሁለት እና ከዚያ በላይ የባለቤትነት ማረጋገጫ ጋር በተገናኙ ክፍተቶች
 
• አላስፈላጊ በሆኑ ፖርቶች እና ግልጽ ወይም ባልተመሳጠረ (ወይም ጠንካራ ባልሆነ ምስጠራ) የግንኙነት ፕሮቶኮሎች ምክንያት
 
• ደህንነታቸው ባልተጠበቀ የመረጃ ቋት
 
• ፊርምዌር (firmware) ወይም ኦፕሬትንግ (operating system) ሲስተምን ለማዘመን ከባድ መሆኑ
 
• ክፍተቶችን ለመዝጋት የአምራቾች ወይም የአቅራቢዎች ድጋፍ አለመኖር
 
• የመሳሪያውን የደህንነት እና የአጠቃቀም አተገባበር ጉድለት
 
• ደህንነታቸው ያልተጠበቀ የሶስተኛ ወገን ክፍሎች መካተት
 
• አካላዊ ስርቆት እና ማጭበርበር የሚሉት ይገኙበታል።
 
 
በመሆኑም ተጠቃሚዎች እየተገለገሉባቸዉ ያሉትን ከ በይነመረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች ላይ ያለዉን አጠቃቀም ስርዓት በማዘመን እና ለሳይበር ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን መከላከል እንደሚገባ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.