Fana: At a Speed of Life!

ብሄራዊ የውሃ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሄራዊ የውሃ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መድረክ ላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ፥ ወቅቱ የሚጠይቀውን የተሻሻለ ፖሊሲ ማዘጋጀት በማስፈለጉ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የሚሻሻለው ፖሊሲ ከወቅቱ የአሰራር ስርዓት ጋር የተጣጣመ፣ ችግር ፈቺ እና አጠቃላይ የሃገሪቱን ቀጣይ የእድገት አቅጣጫ ያማከለ እንዲሆን ታስቦ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ  መሆናቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.