ኢትዮጵያና ጣሊያን የ1 ሚሊየን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጣሊያን ለዜጎች መረጃ ምዝገባ አገልግሎት የሚውል የአንድ ሚሊየን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ተፈራረመዋል፡፡
የእርዳታ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያና ሴሬኒ ተፈራርመውታል፡፡
ሃላፊዎቹ የአገራቱን የልማት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡