የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር የማጠቃለያ ውድድር በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር የማጠቃለያ ውድድር በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ መከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ ከምባታ ዱራሜ፣ ባህር ዳር ከተማ፣ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ ሚዛን አማን፣ ጎንደር ከተማና ድሬዳዋ ከተማ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ናቸው።
በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል ነው የተባለው።
ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ባህር ዳር ከተማን 36 ለ29 ሲያሸንፍ፣ ፌደራል ፖሊስ ሚዛን አማንን 36 ለ 23 ረቷልም ተብሏል።
የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገም ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን፥ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ከያዘው መከላከያ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ መሆኑም ተገልጿል።
በተጨማሪም ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከጎንደር ከተማ ጋር ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የተጠቀሰ ሲሆን÷ የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር የማጠቃለያ ውድድር የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም በሚደረጉ የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ቂርቆስ ክፍለ ከተማና መከላከያ በተመሳሳይ 12 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በቅደም ተከተል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በ11 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ የተገለጸ ሲሆን÷ ድሬዳዋ ከተማ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን 10ኛ ደረጃ ይዟልም ነው የተባለው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!