Fana: At a Speed of Life!

“ብርሃን ለብርሃናማዎቹ ” በሚል የደብረ ብርሃን ከነማ ስፖርት ክለብን ለመደገፍ የተዘጋጀ የንግድ ትርዒትና ባዛር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 130 የሚሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ አምራችና አቅራቢዎች የተሳተፉበት “ብርሃን ለብርሃናማዎቹ ” የተሰኘ ገቢው የደብረ ብርሃን ከነማ ስፖርት ክለብን ለመደገፍ የሚውል የንግድ ትርዒትና ባዛር ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ ተጀምሯል ።

ከንግድ ትርዒቱና ባዛሩ 1 ሚሊየን 500 ሺህ ብር ይገኝበታልም ተብሎ ይጠበቃል ነው የተባለው።

በባዛሩ ላይ ከሀገር ውስጥ አምራቾች በተጨማሪ ከኬንያ፣ ታንዛኒያ ከሕንድ እና ከቱርክ የመጡ 130 ያህል አምራችና አቅራቢዎች ተሳትፈውበታልም ተብሏል።

የደብረ ብርሃን ከነማ ስፖርት ክለብ ፕሬዚዳንት ሰሎሞን አየለ፥ ክለቡ ባለበት የበጀት እጥረት ምክንያት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ሳይሆን ቀርቷልም ነው ያሉት።

አሁን ላይ አቅሙን በማጠናከር የተሻለ ተወዳዳሪ እንዲሆን ነው የንግድ ትርዒትና ባዛሩ የተዘጋጀውም ብለዋል አቶ ሰሎሞን።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ÷ የንግድ ትርዒትና ባዛሩን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን ያለ ደምወዝ ለበርካታ ወራት ትጥቅ ብቻ እየተሟላላቸው የቆዩትን ተጫዋቾች ከጎናቸው በመሆን ማበረታታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩም የተቻለውን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ነው ያመለከቱት፡፡

ለ10 ቀናት የሚቆየው የንግድ ትርኢትና ባዛር 60 ሺህ ያህል ሸማቾች አገልግሎት ያገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል ።

በሳምራዊት የስጋት

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.